ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
73

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውኃና ኢነርጅ ቢሮ  በአንድ ዋሽ ብሄራዊ ፕሮግራም የማስፈጸሚያ በጀት የICT እቃዎች ግዥ (Laptop computer, Desktop Computer, Printers, scanner and other ICT Equipment) በጨረታ ቁጥር ET-AMHARA WIEDB-519738-GO-RFQ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ተጫራቾች ዕቃውን (አገልግሎቶችን ለማቅረብ በዘርፉ አቅራቢነት )ችርቻሮ ንግድ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃና ኢነርጅ ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 27 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ የICT እቃዎች ግዥ (Laptop computer, Desktop Computer, Printers , scanner and other ICT Equipment) ብር 30,000 (ስላሳ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማቅረብ  አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ቴክኒካል (ስፔስፊኬሽን) እና ፋይናንሻል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ ዋናና አንድ ቅጅ ዋናውና ቅጅውን ለየብቻ በማሸግ በድምሩ ሁለት  ፓስታዎች እንዲሁም የጨረታ  ማስከበሪያውን በፖስታ በማሸግ በአንድ እናት ፓስታ በማሸግ በእያንዳንዱ ፓስታ ላይ ፊርማ፣ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የግዡን ስም በመጻፋ በውኃና ኢነርጅ ቢሮ በአንድ ዋሽ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 11 ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን የካቲት 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን የጨረታው መዝጊያ ቀን ደግሞ መጋቢት 8/2018 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን በዚሁ ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውኃና ኢነርጅ ቢሮ በአንድ ዋሽ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን የሚያቀርቡት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ (ቅጽ) መሰረት መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች የመወዳደሪያ የቴክኒካል (ስፔስፊኬሽን) የሚገልጹበት በተሸጠላቸው የጨረታ ሰነድ በተቀመጠው ፎርም መሰረት ይሆናል፡፡
  10. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251 583 20 83 43 /+25158 222 05 79/ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውኃና ኢነርጅ ቢሮ

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here