ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
44

በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የደላንታ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤታችን አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 3. ሌሎች አላቂ የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 4. ቋሚ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 5. ህትመት እንዲሁም ሎት 6. ካባ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው ሁሉም ተጫራቾች በየንግድ ዘርፋቸው ንግድ ፈቃዳቸውን ማቅረብ አለባቸው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ የእቃዎችን አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ደ/ወ/ፍ/ቤት/ግ/ፍ/ን/አስ/ቡድን ክፍል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ (መግዛት) ይችላሉ፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት በጠቅላላ ከሞሉት ዋጋ ላይ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች በደቡብ ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ ቤት ደላንታ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፍ/ን/አስ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 3 ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደላንታ ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፍ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ የማያስተጓጉል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9. የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል (ከስራ ሰዓት ውጪ) ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  10. ጨረታው በሎት ስለሆነ ሁሉም እቃዎች ሳይዘለሉ መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ ሥርዝ ድልዝ ካለው ተቀባይነት የለውም፡፡
  11. ተጫራቾች የሚያቀረቡት ዋጋ የእቃውን መጓጓዣ እና ማንኛውም የመንግስት ታክስን ያካተተ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡ እቃውንም ደላንታ ወረዳ ፍ/ቤት ድረስ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. ተጫራቾች ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዩች በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  1. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፍ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 335 04 30 እና 09 14 33 36 36 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደላንታ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here