በሰሜን ጎጃም አስተዳደር ዞን የደቡብ ሜጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳዉ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኝ ጤና ኬላ አገልግሎት የሚዉል የተቀናጀ የጤና ኬላ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ስለሚፈልግ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፍ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት (ቫት) ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግንባታ ሥራዎች ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾች የታደሰ የግንባታ ብቃት ማረጋገጫ የምስክርት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ከየካቲት 23/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 13/2018 ዓ.ም ባሉት 21 ተከታታይ ቀናቶች ውስጥ በደ/ሜ/ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታውም በ22ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል ነገር ግን 22 ተኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ግንባታ አይነትና የሥራ ዝርዝር ቦታ ፕላንና መመሪያ የያዘ የጨረታ ሰነድ ከመስሪያ ቤታችን ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ሰዓት ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ግንባታ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ መሂ1 ኮፒ ተቆርጦ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከየካቲት 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ እሰከ 22ኛው ቀን 8፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 21ኛው ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ22ኛው ቀን በመ/ቤታችን ግዥ ቢሮ ቁጥር 01 እስከ 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መጋቢት 14/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ለሚያወጡት ወጭ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር +2519 18 22 71 90 በመደወል መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደቡብ ሜጫ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

