በአፈ/ከሳሽ ቲሊሊ ሐርሜላ ሆቴል የሚጣል አፍሪካ የእቁብ ማህበር ዳኞች እነ ደሴ በቀለ እና እሱባለው አዲሱ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ገንዘብ ክስ ክርክር ጉይይ በቲሊሊ ከተማ ቀበሌ 01 አዋሳኙም 1ኛ. አጉማስ ጥሩሰው ንብረት የሆነውን በምሥራቅ ወርቄ ሙሉ፣ በምዕራብ ቄስ አያና አዳም፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ሙሉሰው አዱኛ የሚዋሰነውን ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 984,615.47 (ዘጠኝ መቶ ሰማኒያ አራት ሽህ ስድስት መቶ አስራ ምስት ብር ከአርባ ሰባት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡
2ኛ. የመ/ጌታ ብርሃን ደምሌ ንብረት የሆነውን በምሥራቅ አንዷለም አጥናፍ፣ በምዕራብ ጥላሁን ሞት ባይኖር፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ዓለሙ አዋስኖት የሚገኘውን ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 2,264,415.15 (ሁለት ሚሊዬን ሁለት መቶ ስልሳ አራት ሽህ አራት መቶ አስራ አምስት ብር ከአስራ አምስት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡
3ኛ የነብዩ ጌታቸው ንብረት የሆነው በምሥራቅ ትዕግስት አለኸኝ፣ በምዕራብ አሳዬ ጥላሁን፣ በሰሜን መንገድ እንዲሁም በደቡብ ጥላየ ወርቁ የሚዋስነውን ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,172.704.60 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰባ ሁለት ሽህ ሰባት መቶ አራት ብር ከስልሳ ሳንቲም) ይሸጣል፡፡
4ኛ. የማተቤ አሸንፍ ንብረት የሆነውን በምሥራቅ እና በሰሜን መንገድ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ክንዴ ሰውነት በመነሻ ዋጋ ብር 1,134.102.36 (አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሰላሳ አራት ሽህ አንድ መቶ ሁለት ብር ከሰላሳ ስድስት ሳንቲም) ይሸጣል፡፡ በመሆኑም ሀራጁ ከየካቲት 23/2018 ዓ/ም አስክ መጋቢት 23/2018 ዓ/ም በጋዜጣ ወጥቶ ይቆያል፤ የጨረታ አሸናፊውም ¼ ኛውን ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡ ስለሆነም ሀራጁ መጋቢት 24/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 እስከ 6፡00 በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በቦታው በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡
የአዊ ብሔረሰብ አሥዳደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

