የጨረታ ቁጥር አብክመ/ወኩምኤ/ብ/ግ/ጨ/03/06/2018
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ለተቋም መገልገያ የሚሆን ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በሎት አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አገልግሎቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች (ሎቶች) አንድ በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ከተጠቀሱት ዕቃዎች ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥና ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥ ንብ/አስ/ዳይሪክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 04 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በዓል ወይም የሥራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አገልግሎት መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 406 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 31 58 ፋክስ 058 320 11 83 በመደወል ፖ.ሳ.ቁ 965 በመላክ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ለአገልግሎት

