የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
59

በአፈ/ከሳሽ አቶ አለምሰው ቢያድጉ እና በአፈ/ተከሳሾች እነ አወቀ አያና ደመቀ መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ አፈፃፀም ክርክር ጉዳይ በቲሊሊ ከተማ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ እና በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን ጥላየ ካሴ እንዲሁም በደቡብ የአዱኛው ቤት መካከል የሚገኘውን በ1ኛ በአቶ አወቀ አያና ደመቀ ስም ያለውን የድርጅት ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 2,163,023.42 (ሁለት ሚሊዮን አንድ መቶ ስልሳ ሶስት ሽህ ሃያ ሶስት ብር ከአርባ ሁለት ሳንቲም) በጨረታ ይሸጣል፡፡ በመሆኑም ከየካቲት 23/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 22/2018 ዓ/ም ድረስ በተከታታይ ለ30 ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ መጋቢት 26/07/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ጫረታው ስለሚካሄድ ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 ኛውን ገንዘብ በሲፒኦ በባንክ በማስያዝ ጨረታውን መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ቦታው ድረስ በመቅረብ መጫረት የሚችል መሆኑን እየገለጽን ውጤቱን ለመጋቢት 28/2018 ዓ/ም እንዲገለጽ ሲል ፍ/ቤት አዝዟል፡፡

የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here