የጎንደር ደም ባንክ አገልግሎት በ2018 መደበኛ በጀት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ ዕቃዎችና አገልግሎቶችን ማለትም፡- ሎት 01 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች (ጽ/መሣሪያ)፣ ሎት 02 የቢሮ የእጅ መገልገያ እቃዎች፣ ሎት 03 የታሸገ ዉሃ፣ ሎት 04 ጣፋጭ ክሬም ያለው ብስኩት፣ ሎት 05 ፋንታ ለስላሳ መጠጥ፣ ሎት 06 የተሸከርካሪ ዘይትና ቅባት፣ ሎት 07 ሌሎች አላቂ (የጽዳት ዕቃዎች)፣ ሎት 08 የመኪና ጎማ፣ ሎት 09 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና ሎት 10 ተገጣጣሚ የቢሮ መሳሪያዎች (ፈርኒቸር) እቃዎችን በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸዉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት የሎት የመጫረቻ ጠ/ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተ/እ/ታክስ (ቫት) ከፋይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸዉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር. 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፍል በጎንደር አዘዞ አይራ አካባቢ በሚገኘዉ የጎንደር ደም ባንክ አገልግሎት ዘወትር በስራ ስዓት በአካል በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና መጫረት ይችላሉ፡፡
- የሚቀርቡት የዕቃዎች ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪ ናሙናዎችን ንብረት ክፍል ማየት የሚችሉ ሲሆን የግዥ መጠኑ ከበጀት አንጻር ታይቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት በየሎቱ በቁርጥ 2.000 (ሁለት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ዋናዉን ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ አስቆርጦ ከሚወዳደርበት ሰነድ ጋር አብሮ በማሽግ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ጨረታዉ በጋዜጣ ከሚቆይበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ለተከታታይ 15 ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 3፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በታሸገበት ዕለት 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ወይም በራሳቸዉ ምክንያት ባይገኙም ጨረታዉን በመክፈት እንደስፈላጊነቱ በነጠላ ወይም በሎት ጠ/ዋጋ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት በአሽናፊነት የሚመረጥ ይሆናል፡፡ የጨረታዉ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ሰዓቱ እንደተጠበቀ ሁኖ በቀጣዩ የመጀመሪያ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃና አገልግሎት ዋጋ አዘዞ አይራ ከሚገኘዉ ጎንደር ደም ባንክ አገልግሎት ቢሮ ድረስ ዕቃዉን ለመጓጓዣና እንዲሁም ማንኛዉንም የመንግስት ግብር ወጭ ያካተተ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለቅድመ ምዘና የሚያገለግል መሰረታዊ ሰነድ /የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የሙያ ፈቃድ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተ/እ/ታክስ ከፋይነት ማስረጃዎች እና ፋይናንሻል ሰነድ አዘጋጅቶ በመፈረምና የድርጀቱን ማህተም በማድረግ በጥንቃቄ በፖስታ አሽገዉ እና በፖስታዉ ጀርባ ላይ የሎቱን ቁጥርና ስም በመፃፍ የጨረታ ማስታዎቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘዉትር በሥራ ስዓት በጎንደር አዘዞ አይራ በሚገኘው ደም ባንክ አገልግሎት ጽ/ቤት በተዘጋጀዉ ጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባችዉ፡፡
- ሁሉም ዕቃ ጥራቱን የጠበቀ ኦርጅናል መሆን ይኖርበታል፡፡
- ከጨረታ ሠነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በተለይ ስፔስፊኬሽኑን፣ ናሙና እና የጨረታ መመሪያዉን በማየትና በማንበብ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ቅሬታ ካለዉ ጨረታዉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 5 ተከታታይ የሥራ ቀን ዉስጥ ቅሬታዉን ማቅረብ የሚቻል ሲሆን ከ5 የሥራ ቀናት ዉጭ የሚቀርብ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ፡- ጎንደር አዘዞ አይራ አካባባቢ በሚገኘዉ የጎንደር ደም ባንክ አገልግሎት በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 211 50 52 /09 18 72 55 33 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
የጎንደር ደም ባንክ አገልግሎት

