ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
63

የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/መደ/02/18

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አስተዳደር በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት ውስጥ የሚገኘው የማክስኝት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች ያሉትን ሎቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ ሎት 2. የእንሰሳት መድሀኒት እና የህክምና መሳሪያዎች መሸጫ እቃዎች፣ ሎት 3. የጋርመንት ዕቃዎች፣ ሎት 4. ፀረ ተባይ መድሀኒት እና የግብርና መሳሪያዎች መሸጫ፣ ሎት 5. የእስቴሽነሪ ዕቃዎች፣ ሎት 6. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሎት 7. የጽዳት ዕቃዎች እንዲሁም ሎት 8. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ከሆኑ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  4. የጨረታ ዋጋው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የሚወዳደሩት ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ከሆነ ከመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ኮፒ በማድረግ ኮፒውን ከኦርጅናሉ የመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ዋጋው ለ 15 የስራ ቀናት ይቆያል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ማክሰኝት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡ ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከየካቲት 23/2018 ዓ/ም እስከ መጋቢት 11/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው መጋቢት 12/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡45 ታሽጎ በዚያው እለት ከረፋዱ 4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ በሌሉበት ሰነዱ ተሟልቶ ከተገኘ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኝ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉለው ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ ለተላለፉ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናል፡፡
  11. በጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ አለበት፡፡
  12. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከማክሰኝት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 332 02 76 /09 18 52 94 08 መደወል ይችላሉ፡፡

የማክሰኝት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here