በጎንደር ከተማ አስተዳደር በጤና መምሪያ ሥር የሚገኘው የጎንደር ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች እና ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አውጥቶ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መወዳደር የሚፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከላይ 1-3 የተዘረዘረውን ፎቶ ኮፒ እና ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥውን መጠን እንደአስፈላጊነቱ 20 በመቶ መጨመርና መቀነስ ይችላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከየካቲት 23/2018 እስከ መጋቢት 7/2018ዓ.ም ባለው ተከታታይ ቀን ሰነዱ በሚመለከተው ሰው ተሞልቶ ፊርማና ማህተም ተደርጎበት በጎንደር ጤና ጣቢያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚያበቃው መጋቢት 7/2018 ዓ.ም የሥራ ቀን ሲሆን መጋቢት 08/2018 ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኋላ ናሙና ማቅረብ ወይም ማሳየት ግዴታ አለባቸው፡፡ ናሙና ካልቀረቡ ተቀባይነት የለውም፡፡
- አሸናፊው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት ዕቃውን ተቋሙ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሃሳብ ውድቅ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ለጽዳት እቃ ብር 18,230.64 (አስራ ስምንት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ብር ከ64/100) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ለጽህፈት መሳሪያ እቃዎች ብር 16,380 (አስራ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ሰማንያ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ በመክፈል ጎንደር ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- በድርጅቱ ውስጥ የሌለ እቃ አለኝ ብሎ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ ዝርዝር መሙያ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- አድራሻችን በጎንደር ጤና ጣቢያ በተለምዶ ፖሊ ጤና ጣቢያ ተብሎ በሚጠራው ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ
058 111 06 54 /09 20 34 77 77 በመደውል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- እያንዳንዱ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ የቫት ተመዝጋቢ ካልጨመረ እንደተጨመረ ተደርጎ ስለሚወሰድ በመጨመር ሰነዱ ላይ ይቅረብ፡፡
የጎንደር ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

