ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

0
72

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ስር የሰቆጣ ማረሚያ ቤት መምሪያ ለማረሚያ ቤቱ የህግ ታራሚዎች ምግብ ዝግጅት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእህል አይነቶችን፣ የማገዶ እንጨትና የእህል ምርት ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል ፡፡

  1. በዘርፉ የወጣ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  4. የግዡ መጠን ከ100,000 (ከመቶ ሺ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 -4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በግልፅ በሚታይ ፎቶ ኮፒ
    ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
  6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ለአንድ አመት ተይዞ የሚቆይ የውል ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ
    ሺ ) ብር ማስያዝ የሚችል፡፡
  7. የሚገዙ የእህልና የእህል ምርት ውጤቶች ዝርዝር መግለጫ ስፐስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታ ሰነድ የመሸጫ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከየካቲት 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 7/ 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ነው::
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ በግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 6
    በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. የጨረታ ማስከበሪያ 10,000 (አስር ሽህ ብር ብቻ) ፖስታ ውስጥ አብረው ማሸግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋይ/ንብ/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በ15ኛው ቀን ከጥዋቱ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በ2018 ከጥዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  14. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0914612311 እና በስልክ ቁጥር 0992046895 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል :: አድራሻ – ዋግ ኽምራ ዞን ሰቆጣ ማረቤት ቀበሌ 01

የሰቆጣ ማረሚያ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here