የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ ስለመያዝ በደነገገው አዋጅ 72/2004 መሠረት በ2018 በጀት ዓመት ለ2ኛ ዙር ከ1-6 የተዘረዘሩትን የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ 1ኛ.ቀበሌ 02 በአዋሳኝ በምሥራቅ አጀቡሽ ምትኩ፣ በምዕራብ ዋሲሁን አብተው፣ በሰሜን ዋሲሁን አብተው፣ በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኝ ቦታ ስፋቱ 130.25 ካ/ሜትር ለድርጅት አገልግሎት የሚውል 01 ቦታ፣ 2ኛ. ቀበሌ 02 በአዋሳኝ በምሥራቅ ማስረሻ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ካሳ በለጠ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 90 ካ/ሜትር ለድርጅት አገልግሎት የሚውል 01 ቦታ፣ 3ኛ. ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ ፈንታየ፣ በምዕራብ መንገድ፣ በሰሜን የተመኝ በደቡብ ፔጥሮስ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 252 ካ/ሜትር ቅይጥ 01 ቦታ፣ 4ኛ. ቀበሌ 03 በአዋሳኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ አበባና ሰብለ፣ በሰሜን ወኪል ሙሃመድ፣ በደቡብ ጀማል ኑሪያ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 185 ካ/ሜትር ቅይጥ 01 ቦታ፣ 5ኛ. ቀበሌ 04 በአዋሳኝ በምሥራቅ አዘነጋሽ ባየ፣ በምዕራብ አሰፋሽ ፍቅሬ፣ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ እቴናት በለጠ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 96 ካ/ሜትር ለድርጅት አገልግሎት የሚውል 01 ቦታ እንዲሁም 6ኛ. ቀበሌ 04 በአዋሳኝ በምሥራቅ ቻላቸው አቅናው፣ በምዕራብ፣ በሰሜን እና በደቡብ መንገድ መካከል የሚገኝ ስፋቱ 1824.8 ካ/ሜትር አድሚንስትሬሽን 01 ቦታ ስለዚህ፡-
- የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 17 በመምጣት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ አይነት መደበኛ ነው፡፡
- የጨረታ ሰነድ መግዣ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉበት 10 ተከታታይ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያልቀው በ10ኛው ቀን 11፡30 ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ወ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/ጽ/ቤት ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም (ሲፒኦ) በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ ለድርጅቱ 15 በመቶ ለመኖሪያ 20 በመቶ በማቅረብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ አሸናፊው ከተለየ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- የግንባታ ደረጃ ለድርጅት
- የቦታው አገልግሎት በእያንዳንዱ ምድብ ከሰነዱ ጋር በሚሸጠው ሰነድ ሰንጠረዥ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡
- ለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 446 00 26 ደውለው ማግኝት ይችላሉ፡፡
የወረታ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

