ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
81

በሰሜን ጎጃም ዞን የዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ለማህበረሰቡ ንፅህ የመጠጥ ውሃ ለማቅረብ ሎት 1.የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች እንዲሁም ሎት 2. የትልልቅ መስመሮች የውሃ መገጣጠሚያ እና ሄንስንግ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች ያለዉን መስፈርት አሟልተዉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ የእቃው ግዥ መጠን ከብር 200,000 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀቶችን ከዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ድረስ በዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የዋጋ ማቅረቢያና አስፈላጊ ሰነዶችን ኮፒ በማድረግ በፖስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን ከረፋዱ 3፡30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ እለት 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ግዥፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን ውስጥ ይከፈታል፡፡
  4. ጨረታው ሲከፈት የተወዳዳሪ ድርጅት ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን ባይገኙም በጽ/ቤቱ የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እየገለጽን መክፈቻ ቀኑ ማለትም  በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ለሎት 1. ብር 30,000 እና ለሎት 2. ብር 20,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በሎት ድምር ዋጋ ስለሆነ ተወዳዳሪዎች በመጫረቻ ሰነዱ የተዘረዘረውን ሁሉንም ዝርዝር መሙላት አለባቸው፡፡
  7. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች በራሱ ወጭ ዱርቤቴ ከተማ አስ/ገን/ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡የሚገዙ እቃዎች /አገልግሎቶች ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)፣ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ፡- ዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ግዥ ፋይ/ንብ/አሰተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 223 08 16 /09 74 50 58 99 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here