ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
46

የማዕከላዊ ጎንደር ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የእህል አቅርቦት፣ ፊኖ ዱቄት፣ የምግብ ዘይት እና የዳቦ ማንኳፈፊያ አቅርቦት በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  6. የሚቀርቡ የእህል አቅርቦት፣ ፊኖ ዱቄት፣ የምግብ ዘይት እንዲሁም የዳቦ ማንካፋፊያ አቅርቦት የማቅረቢያ ቦታ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. አሸናፊው በየወሩ እንደ ህግ ታራሚው ብዛት አቅርቦቱ ሊጨምርም ሊቀንስም የሚችል ሲሆን እንዲያቀርብ መምሪያው በሚገልፀው በየ ወሩ የሚቀርብ ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦርድ) ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ከጠቅላላ ዋጋ ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ በገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ገቢ ማድረግ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. የጨረታ ማስታወቂያው የካቲት 30/2018 ዓ/ም ጀምሮ በጋዜጣ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ግ/ፋ/ን አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሠዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከየካቲት 30/2018 ዓ.ም እስከ  መጋቢት 15/2018 ዓም ከረፋዱ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኘበት ሆነ ባይገኙም ጨረታው በሰዓቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  14. ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 73 44 61 ወይም 09 64 79 28 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here