ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ግጨ 03/2018

0
37

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ተሸከርካሪዎች ላይ የሚገጠም GPS በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርቲፊኬት የሚያቀርቡ እንዲሁም የግዥ መጠኑ ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ ቢሮ ቁጥር 101 ወይም 102 በአካል በመቅረብ የማይመለስ የኢትዩጵያ ብር 250 (ሁለት መቶ አምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱን ከገዙ በኋላ  የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመስሪያ ቤቱ  ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፓስታዎች በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን በ15/07/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ፤ በዚሁ ዕለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባህር ዳር ከተማ በሚገኝው የአብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋበት 16ኛው ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች ብር 6,000 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፓስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ወይም አገልግሎት አይነት ቢሮው ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. ጨረታው የሚዘጋበት ቋንቋ በአማርኛ ይሆናል፡፡
  7. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ሙሉ ስፔስፊኬሽን) ፤መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ አብክመ ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኝት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 1356/058 220 0839 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here