ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
55

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሎት 1. የጽሀፈት መሳሪያ፣ ሎት 2. የፕሪንተር ቀለም፣ ሎት 3. የቢሮ የፈርኒቸር እቃ፣ ሎት 4. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 5. የመኪና መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 6. የመኪና ዘይት እና ቅባት፣ ሎት 7. የጀነሬተር መለዋወጫ እቃዎች፣ ሎት 8. የብስክሌት ጎማ ከነካላማዳሪያዉ እንዲሁም የተሸከርካሪ ጥገና የአገልግሎት ግዥ፣ የመኪና ጂፒኤስ ግዥ እና አመታዊ የህትመት የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት እና የሚገዙ እቃዎች ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተገለጹትን መስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የሚገዙ የእቃ እና የአገአልግሎት ግዥ አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ለተሸከርካሪ ጥገናዉ 5,000 (አምስት ሽህ ብር)፣ ለአመታዊ የህትመት ግዥዉ ብር 2,000 (ሁለት ሽህ ብር) ሲሆን ለሌሎች እቃዎች ግን የጠቅላላ ዋጋዉን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም  በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት፡፡
  9. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  10. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ጨረታዉ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 218 00 14 /058 218 11 03 ደውለው መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡

አብክመ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here