የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2018 በጀት አመት ሎት1. የጽህፈት መሳሪያ ፣ሎት2. የጽዳት ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው ፤ነገር ግን ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቶች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ገንዘብ ያዥ ቢሮ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ እና ንብረት አስተዳዳር ቡድን በቢሮው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከየካቲት 30 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን መጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሶስተኛ ፎቅ ግዥ ቡድን ይከፈታል፡፡ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጠ/ፍ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 02 56 65 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት

