በአፈ/ከሳሽ መሳፍንት ቢረሳው ማህበር እና በአፈ/ተከሳሽ አቶ መንግስቱ ካሳሁን መካከል ባለዉ የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ 008፣ በምዕራብ 006፣ በሰሜን እና በደቡብ መንገድ መካከል የሚያዋስን በአፈ/ተከሳሽ መንግስቱ ካሳሁን ስም ተመዝግቦ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት በመነሻ ዋጋ ብር 1,490,000 (አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና ሺህ ብር) ይሸጣል፡፡ በመሆኑም የጨረታ ማስታወቂያ በ30 ተከታታይ ቀናት ማለትም የካቲት 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 30/2018 ድረስ በጋዜጣ ወጥቶ ቆይቶ በመጋቢት 30/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3:00 እስከ 6፡00 ስለሚሸጥ ተጫራቾችም ከጨረታ ቀን በፊት የሚጫረተውን ንብረት መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በሲፒኦ አስይዘው በመቅረብ መጫረት ይችላሉ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

