ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
56

የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለማስተማሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ ዕቃዋችን ለ2ኛ ጊዜ በጨረታ አወዳድሮ ጥቅል ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት፡- 1. የህንጻ መሳሪያ ዕቃዎች፣ 2. የኤሌክትሮኒክስ እና የኮምፒዩተር ዕቃዎች፣ 3. የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ 4. የጋርመንት ዕቃዎች እንዲሁም 5. የጽዳት ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ለመወዳደር የምትፈልጉ የመወዳደሪያ ሰነዱን ከመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 2  የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝታችሁ በመውሰድ የምትሸጡበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 2 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን እንድታስገቡ ይጋብዛል፡፡

  1. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
  2. ጨረታው የሚከፈተው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 2 ይከፈታል፡፡ በእለቱ ካልተገኙ ግን ጨረታው በኮሚቴ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለህንጻ መሳሪያ ብር 2,000፣ የኤሌክትሮኒክስና የኮምፒዉተር ዕቃዎች 5,000፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች 2,000፣ የጋርመንት ዕቃዎች 8,000 እና የጽዳት ዕቃዎች 2,000 በጥሬ ገንዘብ በኮሌጁ የገቢ ደረሰኝ በመቁረጥ ወይም በሲፒኦ በማስያዝ ከጨረታው ፖስታ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ የሥራ ፈቃድ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ከመጫረቻ ፖስታው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የመጫራቻቸው ጠቅላላ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የእቃውን ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከተቀመጠው ስፔስፊኬሽን ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡ እንዲሁም ሥርዝ ድልዝ ካለው ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ መመሪያ የመግዛት ግዴታ አለባቸው፡፡
  8. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት (በድምር ዋጋ) በሞሉት ነዉ፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 058 771 26 32 /058 7716 93 /058 771 71 24 /058 771 50 28 /058 771 71 69 /058 771 70 27 በመደወል  መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደብረ ማርቆስ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here