በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የታደሠ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ቲን ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሆነው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ለእቃው ቀጥተኛ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ 200 ብር በመያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት ማለትም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 102 ሠነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በኦርጅናሉ የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት የካቲት 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት፤ መጋቢት 12/2018 ዓ.ም 6፡30 ታሽጎ መጋቢት 14/2018 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጨረታው ከሚቀርቡ አገልግሎት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ ሁለት በመቶ በባንክ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ዋጋ የሚሞላውና ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው፡፡
- በጨረታው የሚሳተፈው ተወካይ ከሆነ ህጋዊ የሆነ ውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፤ተጫራቾች በወቅቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታዉ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾለት ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ እቃውን ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 058 218 1424 /058 218 0644 /058 218 0075 መጠየቅ ይቻላል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅ/ጽ/ቤት

