ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ አማካኝነት ለውኃ ልማት ጽ/ቤት፣ ለእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት መምሪያ፣ ለግብርና መምሪያ የመስኖ ካናል ግንባታ ማስገንባት እና የተለያዩ ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 የውኃ እቃ፣ ሎት 2 የእንቁላል ጣይ ደሮ፣ ሎት 3 የደሮ መኖ፣ ሎት 4 የእንስሳት መድሀኒት እንዲሁም ሎት 5 የመስኖ ካናል ግንባታ ሲሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ በተጠቀሰው የጨረታ ዓይነት በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፡፡
  2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. ያቀረበው ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የተዘረዘሩትን መረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ማቴሪያሎችን ዝርዝር መግለጫ (ሰፔስፊሌሽን) ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሚወዳደሩበት የዕቃዎች ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም ደብረ ታቦር ከተማ አስ/ገን/መምሪያ በጥሬ ገንዘብ በመሂ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ኮፒ እና ኦርጅናል ሥርዝ ድልዝ በሌለበት የተጫራቾችን ስም ፊርማ፣ ማህተም ጨረታው ያወጣው መ/ቤት ስምና አድራሻ በመግለፅ በደ/ታ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን ድረስ ባሉት ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡10 ይከፈታል፡፡
  9. በጋዜጣ የወጣው ጨረታ የሚከፈትበት እለት በዓል ቀን ከሆነ ጨረታው የሚታሸገውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀንና ሰዓቱን ጠብቆ ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  11. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በተመለከተው መሰረት የእያንዳንዱን ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መግለጽ አለባቸው፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች ከነጠላም ዋጋ ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ላይ በተጫራቾች ላይ የሚሞላ ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ ቢሆንም ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  13. በማንኛውም ሁኔታ ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ (ተመስርቶ) መጫረት አይችሉም፡፡
  14. የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፣
  15. ውድድሩ በሎት ስለሆነ አንደም እቃ ሳይሟላ መቅረብ የለበትም ሳያሟላ ከተገኘ ከውድድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
  16. የእቃው መጠን እስከ 20 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
  17. መምሪያው በጨረታ ሰነድ ላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ የመረጠውን ዓይነት የመግዛት መብት አለው፡፡
  18. እቃው የሚቀርብበት ቦታ ደ/ታ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ ድረስ ይሆናል፡፡
  19. ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  21. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ደ/ከ/አስ/ገን/መምሪያ/ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 ወይም በስልክ ቁጥር 058 441 02 09 /058 141 93 75 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here