ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
58

በደቡብ ጎንደር ዞን የፎገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለፎ/ወ ግብርና ጽ/ቤት በወረዳችን  ቲዋ-ዛቀና እና አቧ ኮኪት ቀበሌ ሚዚዋ ወንዝ ከወረዳው 2.5 ኪ.ሜ ርቀት ያለው ሲሆን ለጎርፍ መከላከል ደለል ማውጣት እና የዳይክ ሥራ ለማሰራት ኤክስካቫተር ባለሰንሰለቱ ከነ-ነዳጅ ለ667 ሰዓት ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የፎ/ወ/ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት ከመነጉዘር-አባጉዳ ቀበሌ ዶዘር ከነ-ነዳጁ 100 ሰዓት እና ከወጅ-አዲስ ቤተክርስቲያን ቀበሌ ግሬደር ከነ-ነዳጁ  100 ሰዓት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ማንኛውንም ወጭ በጨረታ አሸናፊዉ የሚሸፈን ሲሆን መወዳደር የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ለምዝገባ በሚመጡበት ወቅት የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ፡-

  1. በዘመኑ የታደሠ በዘርፋ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ካርድ ያላቸው፡፡
  2. የጨረታ መጠኑ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በፎ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ግዥ ቡድን በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻ በትክክል በመሙላትና በደንብ ፖስታውን በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር በማድረግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት (ሲፒኦ) ወይም በጽ/ቤታችን ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ለኤክስካቫተሩ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር)፤ ለግሬደር እና ለዶዘር ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሁኖ ይቆይና 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. 16ኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና በዚሁ እለት በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  6. አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  7. ሰነዱን ለሚገዙ ተጫራቾች ዝርዝርና (ስፔስፊኬሽን) ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡
  8. የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊው ድርጅት ውል እንደያዘ ጨረታ ላላሸነፋት አካላት ተመላሽ ይሆናል፡፡
  9. አንድ ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ ተተንርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  10. የማሽን ሊቭሪ ኮፒ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ እና አሸናፊዉ አካል ለዉል ሲመጡ ኦሪጂናል ሊብሪ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. አሸናፊው በውሉ መሠረት ካልሰሩ መ/ቤቱ በግዥ መመሪያው መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን መረዳት ይኖርበታል፡፡
  12. አሸናፊ የሚለየው በየሰነዱ በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡
  13. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 446 20 26 በመደወል ጠይቀው መረዳት ይችላሉ፡፡

የፎገራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here