የቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ቡድን በወረዳው ለሚገኙ ሴ/መስሪያ ቤቶች ለ2018 የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እንዲሁም ሎት 2 የመኪና መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊ ለይቶ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- ግዥዉ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚፈለገውን የእቃ አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊክሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመሂ 1 የተቆረጠ ጥረ ገንዘብ ደረሰኝ ኮፒ አድርገው በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ቋ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ከመጋቢት 07/2018 እስከ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም 12፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቋ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በቀን መጋቢት 22/2018 ዓ/ም 3:30 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቋ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 መጋቢት 22/2018 ዓ/ም 4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ ስማቸውንና ፊርማቸው የድርጅቱ ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባችኋል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 271 00 31 /02 69 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፦ የመክፈቻ ቀን ሎት 1 የጽህፍት መሳሪያ በቀን መጋቢት 16/2018 ዓ/ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
ሎት 2. መኪና መለዋጫ መጋቢት 16/2018 ዓ/ም 9፡30 ታሽጎ 10፡00 ይክፈታል፡፡
የቋራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

