በከፈ/ከሳሽ አበበ ተላከ እና በአፈ/ተከሳሽ ሙሉቀን አንዳለው መካከል ስለአለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በአፈጻጸም ተነሣሽ ባለቤት ወ/ሮ እቴነሽ ፈቃዱ ስም ተመዝግቦ የሚገኘው በዳንግላ ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ በአዋሣኝ በምሥራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ቦታ ቁጥር 232 ፣ በሰሜን ቦታ ቁጥር 325 እንዲሁም በደቡብ ቦታ ቁጥር 329 የሆነውን በመነሻ ዋጋ ብር 3,825,000 (ሶስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃያ አምስት ሽህ ብር) በማድረግ የጨረታ ማስታወቂያዉን ከመጋቢት 07/2018 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም በጋዜጣ እንዲዉል በማድረግ ማያዚያ 07/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በጨረታ ይሸጣል፡፡ በመሆኑም የጨረታ አሸናፊው የአሸነፈበትን ¼ ኛውን ወዲያውኑ በፍ/ቤቱ አማራ ባንክ አካውንት ቁጥር 9917292928 ገቢ እንዲያደርጉ እና ቀሪውን ገንዘብ ደግሞ ውጤት በሚገለጽበት ቀን ይዞ መቅረብ አለበት፡፡ ስለሆነም መግዛት የሚፈልግ በቦታው በመገኘት መጫረት የሚችል መሆኑን ፍ/ቤቱ አስታውቋል፡፡
የአዊ ብሔረሰብ ዞን ከፍ/ቤት

