ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
36

በደቡብ ወሎ ዞን በጊምባ ከተማ አስተዳደር የጭሮ ከተማ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት ዓመት የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት የማሽን ኪራይ ይፈልጋል፡፡ 1ኛ. የማሽኑ ስም ሞተር ግሬደር፣ ብዛት 1፣የማሽኑ አይነት 140 HP እና ከዚያ በላይ ከ2008 እ.ኤ.አ ወዲህ የተመረተ፣ 2ኛ. ኤክስካቫተር ብዛት 1፣የማሽኑ አይነት 325 HP እና ከዚያ በላይ ከ2008 እ.ኤ.አ ወዲህ የተመረተ፣ 3ኛ.ኤክስካቫተር በጃክ ሃመር፣ብዛት1፣የማሸኑ አይነት 325 HP እና ከዚያ በላይ ከ2008 እ.ኤ.አ ወዲህ የተመረተ፣ 4ኛ.ኮምፖክተር (ሮሎ) ፣ብዛት 1 ፣የማሽኑ አይነት ከ14 ቶን አና ከዚያ በላይ ከ2008 እ.ኤ.አ ወዲህ የተመረተ፣ 5ኛ.ዳምፕትራክ ብዛት8 ፣የማሽኑ አይነት ከ16 ሚ.ኬ እና ከዚያ በላይ የሚይዝ ፣6ኛ.የውሃ ቦቲ (ሻወርትራክ) ፣የማሽኑ አይነት 10,000 ሊትር እና ከዚያ በላይ የሚይዝ ፣7ኛ.ሎደር ፣ብዛት1 ፣የማሽኑ አይነት አካፋው 3ሜ.ኪ እና ከዚያ በላይ ከ2008 እ.ኤ.አ ወዲህ የተመረተ፡፡ የተጠቀሱትን ማሽኖች ከ2008 እ.ኤ.አ ወዲህ የተመረተ ምርት ማቅረብ የምትችሉ፡፡ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት  መወዳደር ትችላላችሁ ::

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥ መጠን ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. እያንዳንዱ ዋጋ የሚሞላው በነፃ ገበያ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት ፡፡
  4. ተጫራቾች የማሽን የቴክኒክ ብልሽት ፣ የስፔር ፓርት ለውጥ እንዲሁም ዘይት ነክ ነገሮች እና የነዳጅ ወጭዎች በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  5. የማሽን ኪራይ ሰዓት የሚያዘው ለስራው ስራ ሰዓት ብቻ ነው (የተፈጥሮ አደጋዎች ዝናብ እና ተያያዥ ችግሮች ከተከሰቱ የሚባክነው ሰዓት አይያዝም)፡፡
  6. ስራ ለማስጀመር የማሽን መጓጓዣ እና መጫን ማውረድ ፤ እንድሁም ስራ ከተጀመረ ቡኋላ ማሽኖችን ከሚሰሩበት ቦታ (ሳይት) ወደ ሌላ ሳይት ወይም የገረጋንቲ ማምረቻ ቦታ ማንቀሳቀስ ቢያስፈልግ (ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ግሬደር፣ ቫይብራቶሪ ሮለር ወዘተ ከጭሮ ከተማ እስከ 5 ኪ.ሜ ርቀት በሁሉም አቅጣጫ) መጓጓዣና መጫኛ ማውረጃ ተጫራቹ የሚችል ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የሹፌር እና የኦፕሬተር እንዲሁም የረዳት አበል እና ሌሎች ወጭዎች ተጫራቹ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 17 የተጠቀሱትን ለሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  9. የዕቃው ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  10. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃውን የያዘውን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ)  በመክፈል ከጭሮ ከተማ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመሂ 1 ማስያዝ ያለባቸውና የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተፃፈለት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውል መግባት ያለባቸው ሲሆን የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን እና ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ኦርጅናል ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ጨረታ ከወጣበት ቀን ከመጋቢት 7/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሰራ ቀናት ማለትም እስከ መጋቢት 28/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ ሰነዱን መሙላትና በ16ኛው የስራ ቀን ማለትም መጋቢት 29/ 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ3:00 እስከ 6:30 ድረስ በጭሮ ከተማ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት በመገኘት መመለስ ወይም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ታትሞ ቆይቶ በ16ኛው ቀን በ6፡30 ይዘጋል፡፡ በዚሁ ቀን ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡00  ይከፈታል ፤ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  14. መ/ቤቱ በጨረታው የሚሰሩ ስራዎች ላይ ብዛት የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  15. ማንኛውም ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም ፡፡
  16. ማንኛውም ተጫራቾች ግዥው በጥቅል (በሎት) የሚፈፀም መሆኑን አውቆ ለእያንዳንዱ ዝርዝር እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በሙሉ ጠቅላላ እያንዳንዳቸው ዋጋ አለመሙላት ከጨረታው ውድቅ ይደርጋል ፡፡ ሆኖም ግን ግዥው በጥቅል ወይም በሎት ቢሆንም መ/ቤቱ የተጋነነ ዋጋ የተሞላባቸው ስራዎች ካሉት ውስጥ ነጥሎ በማውጣት ዝቅተኛ ዋጋ ካቀረቡት አቅራቢዎች በለቀማ ማሰራት እንደሚቻል መታወቅ አለበት ፡፡ እንዲሁም አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ስራዎች ሙሉ በሙሉ ሰርቶ ካላስረከበ ክፍያ አይፈጸምም፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  18. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 09 29 38 69 17 /09 26 21 42 በመደወል ማግኘት ይችላለ፡፡

ማሳሰቢያ ፡- ወደ ስራ ከገቡ በኋላ ናፍጣ የሚሞላው በተቋራጩ ይሆናል፣ ከመንገዱ እስከ ኳሪ ሳይት ያለው ርቀት ከ 0 እስከ 5 ኪ.ሜ መሆን አለበት፡፡

የጭሮ ከተማ ንኡስ ማዘጋጃ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here