ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
45

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአምባጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በከ/መ/ል/ጽ/ቤት ስም ለሚያሰራው የኮሪደር የጠጠር መንገድ ስራ ጥራቱን የጠበቀ ጋራጋንቲ እራሱ አምርቶ በሜትር ኪውብይክ በማቅረብ ከቦታው ድረስ ደፍቶና በትኖ የመጠቅጠቅ ስራ የሚሰራ ፤ቦታውም ከሃይስኩል ት/ቤት እስከ ሳቅደብር መገንጠያ ከአስፓልቱ ዳር ለዳር ለሚሰራው የኮሪደር ልማት ስራ  ማቅረብ የሚችሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬትና በመንገድ ስራው የስራና የመልካም ስራ አፈፃፀም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ኦርጅናል ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. በመንገድ ስራ ኮንስትራክሽን /WWC/ደረጃ7እናከዚያበላይ የሙያፍቃድ ያለው/ያላት
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የሚገዙ ዕቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና ናሙና የሚያስፈልጋቸው ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ከአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን ሥርዝ ድልዝ ወይም በፉልዱ የተስተካከለ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
  10. የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በተናጠል በየሎት ምድባቸው የሚለይ ይሆናል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን /ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  12. በጨረታው 1ኛ የወጣውን ውል እስከ ሚወስድ ድረስ 2ኛ የወጣው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም፡፡
  13. አሸናፊው አሸናፊነቱን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሥዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት መጋቢት 07/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታውን መግዛት ይችላል፡፡
  15. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን መጋቢት 22/2018 ዓ/ም በተዘጋጀው ሳጥን ከረፋዱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አያግደውም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን ይከፈታል፡፡
  16. መ/ቤቱ ከቀረበው አጠቃላይ የሥራ መጠን ዋጋ ላይ እስከ 20 በመቶ መቀነስ እና መጨመር ይችላል፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  18. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 118 08 46 /09 35 28 46 02 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአምባጊዮርስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here