በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን በደብረ ታቦር ከተማ አስተዳደር የጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ኃ.የተወሰነ ህ/ስ/ማህበራት ዩኒዬን ለ2018/2019 የምርት ዘመን ወደ ተለያዩ ዞን፣ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ለሚሰራጨው የምርጥ ዘር ትራንስፖርት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ (ሲፒኦ) ከታወቀ ባንክ /በጥሬው/ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የባለቤትነት ንብረት ሊብሪ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ለእያንዳንዱ የሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጉና የዘር ብዜትና ግብይት ኃላፊነቱ ተወሰነ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን በሚገኝበት ደብረታቦር ከተማ ቀበሌ 02 ደሴት ላይ ቡና ባንክ ፒተር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ምርጥ ዘር ኩንታል ብዛትና የሚሰራጭበትን የቦታ ዝርዝር መገለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ ታሽጎ ጉና ዘር ብዜትና ግብይት ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን በሚገኝበት ደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን ደብረታቦር ከተማ ቀበሌ 02 ደሴት ላይ ከሚገኘው ፒተር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ቅዳሜን ጨምሮ ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከመጋቢት 07/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛ ቀን መጋቢት 18/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ (ታሽጎ) በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ እለት በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው ተመሳሳይ የስራ ቀንና ሰዓት ይዛወራል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል በታሸገ ፖስታ (ኢንቨሎፕ) በጥንቃቄ በማሸግ የድርጅቱን ክብ ማህተም ተደርጎበት በዩኔዬኑ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ለማግኘት 09 30 70 99 26 /09 79 26 13 56 /09 18 21 87 40 /09 18 01 85 02 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሌሎች ያልተካቱ ሁኔታዎች ካሉ በውስጥ ማስታወቂያ ይገለፃሉ፡፡
- የሚሰራጨው ምርጥ ዘር በሚወስዱት ማህበራት ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ሊጨምርም ሊቀንስም እንደሚችል ታሳቢ ይደረግ፡፡
- ዩኒየኑ አሸናፊውን የሚለየው በነጠላ ዋጋ ውጤት ነው፡፡ ይህም በዩኒየኑ ግዥንና ሽያጭ መመሪያ መሰረት የሚፈፀም የሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ለማግኘት 09 30 70 99 26 /09 79 26 13 56 /09 18 21 87 40 /09 18 01 85 02 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጉና ዘር ብዜት እና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዬን

