ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
115

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃየተ ሎት 1 ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ በቡሬ ደምበጫና ፍ/ሰላም ከተሞች መጋዝን፣ ቢሮ፣ የጥበቃ ቤት፣ የመጸዳጃ ቤትና የአጥር ግንባታ የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ግንባታውን ለማስገንባት የአካባቢ ተጽዕኖ ግምግማ ጥናት ለማሰራት አስፈላጊውን የሰው ኃይል ህትመቶችን አቅርቦት አሟልተው መወዳደርና መስራት የሚፈልጉ የሀገር ውስጥ አማካሪዎችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ሎት 2 ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የ2018 ዓ/ም ምርት ዘመን 5,000 ሽህ ኩ/ል የስንዴ ሰብል ሽያጭ፣ ሎት 3 ለአራተኛ ጊዜ የወጣ ከቡሬ ከተማ ወደ ወረታ ከተማ 17,300 ኩ/ል ሰብል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የደረቅ ጭነት ደረጃ 4 እና ከዚያ በላይ የሆነ እንዲሁም ሌብሬ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የኦፕሬተር ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ማቅረብና ማያያዝ የሚችሉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. ለማማከር አገልግሎት የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለ2018 ዓ/ም የታደሰ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆነ አማካሪዎች የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው የንግድ ፈቃድ እንዲሁም የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) የቫት ምዝገባ መለያ ቁጥር (ቫት) ሠርተፊኬት 6 ወራት ያልሞላው የቫት ክሊራንስ የዘመኑን ግብር ስለመገበራቸው የሚያሳይ የግብር ክሊራንስ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የሚያሳይ ሰርተፊኬት በአካባቢው ተጽዕኖ ግምገማና ተዛማች ስራ ቢያንስ አንድ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የሚሞሉት የጨረታ ዋጋ 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም የሚሞሉት ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለበት፡፡
  2. በዚህ የመማክር ጨረታ መሳተፍ የሚችሉት አማካሪዎች በዘርፉ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየኑ ግዥና ፋይናንስ ዲቪጅን መውሰድና ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በሁለት ኮፒ ዋና እና ኦርጅናል አያይዘው በማሽግ ማቅረብና ፖስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. በውክልናው የሚጫረቱ ተጫራቾች ግልጽና የማያሻማ ውክልና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም የጨረታ ኮሚቴው በውክልናው ላይ ጥርጣሬ ካደረበት ተጨማሪ ማስረጃ ሊጠይቅ ወይም ሊያጣራ ይችላል፡፡
  5. አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች በቀረበው የስራ ዝርዝር መሰረት ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ነው፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 8ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እና በ8ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ የመክፈቻ ቀን በእለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው  አይስተጓጓለም፡፡
  8. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች በራሱ ስም የተዘጋጀ የማጓጓዣ ሰነድ (ዲስፓች) ማዘጋጀት አለባቸው፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የመንገድ፣ የወዛደርና የቀረጽ ወጭዎችን መሸፈን አለበት፡፡
  11. አሸናፊ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው እንደተገለጸላቸው በኢትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የደንብ ዋስትና የተወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ማስከበሪያ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቶ ገቢ ይሆናል፡፡
  12. ለስንዴ ሽያጭ ሎት 2 የማንሻ ቦታ ቡሬ ከተማ 04 ቀበሌ የሚገኘው መጋዝን ሲሆን የመጫኛና ልዩ ልዩ ወጪዎችን ገዥ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  13. በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥ እና ሽያጭ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
  15. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- የመክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀንና ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃየተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here