የጨረታ ቁጥር፡ ጢእ/አካ/01/2026
ኩባንያችን ጢስ እሳት ዉሀ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚሰጡ ሚክስሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩና በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በጨረታዉ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
| ተ.ቁ | የእቃዉ (የጥገናዉ) አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ | ምርመራ |
| 1 | 750 ሊትር ሚክሰር ጥገና | ብር 20,000 | ኢንጅን እና ጊር ቦክስ ጥገና |
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የቲን ሰርተፊኬት ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 9፡30 ባሕር ዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናዉ መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በኩባንያችን አባይ ማዶ ቴዲ የአሸከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናዉ መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 011 ግዥ መምሪያ በነጻ (ያለ ክፍያ) መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በተቀመጠዉ በሰንጠረዥ መሰረት ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚያወጡት ወጪ በተጫራቹ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸዉን እና የጨረታ ማስከበሪያዉን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ለእያንዳንዱ የጥገና ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትክክል ሞልተው በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ PR-03/2017 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀዉ መጠን 25 በመቶ ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊዉ ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ዉስጥ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (Unconclitional Bank Guarantee) በማሰራት ዉል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
- የማቅረቢያ ጊዜ (የጥገና ጊዜ ) እንደ አስፈላጊነቱ በስምምነት የሚወሰን ይሆናል፡፡ የአቅራቢዎች ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት፡፡
- ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማሳሰቢያ፡- እንደ ኩባንያችን ፍላጎት ዉድድሩ በሎት ወይም በእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ መሠረት ሊሆን ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058 220 48 26 /058 320 25 48 ወይም በፋክስ ቁጥራችን 058 220 48 30 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ጢስ እሳት ዉሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ባሕር ዳር

