ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
16

በምዕራብ ጎጃም ዞን በቡሬ ከተማ የዕድገት በአንድነት የዘር ብዜትና ግብይት ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ/የተ ሎት 1. ምርጥ ዘር በቆሎ በተመደበበት ወረዳ ማጓጓዝ እንዲሁም ሎት 2. 12×24 አንደኛ ደረጃ ኮርያ ምርት ሸራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ለጨረታው የቀረበውን ዝርዝር መረጃ በጨረታው ሰነድ ላይ ያገኛል፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
  4. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዩኒየኑ ሂሳብ ክፍል መግዛት ይችላል፡፡
  5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደርበት ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ሲሆን በጥሬ ገንዝብ ወይም በሚጫረቱበት ሰዓት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ያለበለዚያ የጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ፎቶ ኮፒና በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ኦርጅናል ከሆነ ደግሞ ከፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረብያ ሰነዱ ላይ ስልጣን ባለው አካል የተፈረመበት እና የድርጅቱ ማህተም የተደረገበት መሆኑን በማረጋገጥ እና በፖስታ ላይ 3 ቦታ ማህተም ማድረግ በማሸግ ዩኒየኑ ጽ/ቤት በተዘጋጀው ትራንስፖርት ለማጓጓዝ 7 ቀን ለተከታታይ የሥራ ቀን ከቀን ከመጋቢት 14/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 21/2018 ዓ.ም በሥራ ሰዓት እስከ 11፡30 ማስገባት ሲችሉ ጨረታው የሚከፈትበት መጋቢት 22/2018 ዓ/ም 4፡30 ለሸራ ግዥ ለ10 ለተከታታይ የስራ ቀን መጋቢት 14/2018 ዓ/ም እስከ መጋቢት 24/2018 ዓ/ም በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ማስገባት ሲችሉ ጨረታው የሚከፈትበት መጋቢት 25/2018 ዓ/ም 4፡30 ነው፡፡
  7. ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይስተጓጎልም፡፡ ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ጨረታው በተከፈተ እና አሸናፊነቱ በተገለፀበት ቀን ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀን የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፈበት ዋጋ 10 በመቶ ውል መያዝ አለበት፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  8. ተጫራቾች ዩኒየኑ ለሚከፍለው ክፍያ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን ሙሉ በሙሉ ማሟላት አለባቸው፡፡
  10. ዩንየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  12. ተጫራቾች 145 ኩንታል የመጫን አቅም ያለው ወይም ከዛ በላይ ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡
  13. ለበለጠ መርጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 12 31 74 50 /09 42 74 29 93 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ አድራሻ ቡሬ ከተማ ከዳሞት ዩኒዮን 600 ሜትር ወረድ ብሎ ወይም ከኢንዱስትሪ ፓርኩ ጎን ነው፡፡

የአንድነት የዘር ብዜትና ግብይት ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ/የተ.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here