የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት በብ/የሚ/የግ/ግክ/ቡድን በ2018 በጀት አመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶች ማለትም፡- የደን ዘር፣ የአትክልት ዘር፣ የደጋ ፍራፍሬ እንዲሁም ፖሊቲሊን ቲዩብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የተለያዩ ግብዓቶች ማለትም፡ ሎት 1. የደን ዘር (ጌሾ 150 ኪ/ግ ግራቪሊያ 40 ኪ/ግ እና ወይራ 20 ኪ/ግ) ሁኖ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና ከኳራንታይን የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ሎት 2. የአትክልት ዘር (ቀይስር 8.5 ኪ/ግ ዝርያው ዳትሮይድ ዳርክሬድ፣ ካሮት 8 ኪ/ግ ዝርያው ናንተስ፣ ጥቅል ጎመን 75 ኪ/ግ ዝርያው ኩፕን ሀገን ፈረንጅ ቀይ ሽንኩርት 8.5 ኪ/ግ ዝርያው አዳማሬድ፣ ቲማቲም 1.5 ኪ/ግ ዝርያው መልሳሳልሳ የሆነ የብቃት ማረጋገጫ ስርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ሎት 3. የደጋ ፍራፍሬ (አፕል የተጣበቀ በቁጥር 1875 ዝርያው ቢአር) ሁኖ የችግኙ ቁመት 1.3 ሜትር እና ተስተካከሎ ቀጥ ብሎ የወጣ የከተባ ቦታው ከመሬት በላይ ከ20-30 ሴ/ሜ ከፍታ ላይ የሆነ፣ ችግኙ በሁሉም አቅጣጫ ስር ያለው፣ ከበሽታ እና ተባይ የፀዳ እና ከኳራንታይን የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣ ሎት 4. ፕላስቲክ ወይም ፖሊቲሊን ቲዩብ 3 ኩ/ል ዲያሜትሩ ባለ 10 ሴ/ሜ እና ነጭ የሆነ፣ ፕላስቲክ 3 ኩ/ል ዲያሜትሩ 14 ሴ/ሜ ጥቁር የሆነ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ፣ የአሰሪው መ/ቤት እና የተጫራቹ ሙሉ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ ማህተም በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት በያአንዳንዱ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል ከቢቡኝ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት ደ/ሂ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢ/ወ/ግ/ጽ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከመጋቢት 14/2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት 28/2018 ዓ.ም 10፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን 10፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግብ/ፅ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን በቢሮ ቁጥር 06 መጋቢት 29/2018 ዓ.ም 3፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀበት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን 20 በመቶ የመጨመርም የመቀነስም መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሚከፍትበት ቀን በዓል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ግብዓቱ የሚቀርበው በሙሉ ቢ/ወ/ግ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ሲሆን በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኝት ወይም በስልክ ቁጥር 058 254 06 04 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
የቢቡኝ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት

