የአዲስ ዘመን ከተማ አስተዳደር ከተማ መሠረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መሠረት በ2018 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ የድርጅት 3፣ ለመኖሪያ 2፣ ጠቅላላ 5 ቦታዎችን ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በከተማ መሠረተ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ከጧቱ በ3፡00 ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 18 31 73 72 ወይም 09 23 41 83 38 መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአዲስ ዘመን ከ/አስ/ከ/መሰ/ል/ ጽ/ቤት

