ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
21

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያዎች እና ሎት 2. የፎቶ ኮፒና የፕሪንተር ቀለም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፡፡
  2. የግዥ መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሰክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ የዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን  የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 003 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋሰትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋሰትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር  በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የሚቀርበዉ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ በሚል ስም ተዘጋጅቶ  መቅረብ  አለበት፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታዎች በማድረግ በአብክመ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ በግዥ /ፋይ/ንብ /አስ/ ዳይሬክቶሬት የግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ቁጥር 07 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ የቴክኒካል ፖስታው ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ አሽገው ዶክመንቱ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  9. ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን 3፡30 ይታሸግና ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻዉ ዕለት የህዝብ በዓል እና ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን ከረፋዱ  4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
  1. አሸናፊዉ ድርጅት የሚመረጠዉ በጠቅላላ ዋጋ (በሎት) ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ይሆናል፡፡
  1. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  1. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 07 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 18 84 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 63 50 /058 320 86 86 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አብክመ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here