በአፈ/ከሳሽ አበበ ታከለ እና ጓደኞቹ የእቁብ ማህበር እና በአፈ/ተከሳሾች 1ኛ.አቶ መብራት አጣናው አድማስ፣ 2ኛ.አቶ ይበልጣል ዩሃንስ አድማስ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ ፤በቁጭ ከተማ ቀበሌ 01 ውስጥ የሚገኘውን እና በአቶ መብራት አጣናው ስም ተመዝግቦ የሚገኝ፤ የካርታ ቁጥር 514/2007 የሆነ፤ በምስራቅ የንጉሴ ግርማ፣ በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን ደምስ አላምረው ፣እንዲሁም በደቡብ ደግሰው መካከል ተዋስኖ የሚገኘው 116.5 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ቤት ፤በመነሻ ዋጋው 582,270 (አምስት መቶ ሰማንያ ሁለት ሽህ ሁለት መቶ ሰባ) ብር ሚያዚያ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡30 ድረስ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለሆነም ማንኛውመ ተጫራች ቤቱ በሚገኝበት በቁጭ ከተማ ቀበሌ 01 በመገኘት ፤ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ፤ጨረታውን ያሸነፈው ግለሰብ ያሸነፈበትን ዋጋ ¼ኛውን በሞዴለ 85 ጨረታው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ የሚያስይዝ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት

