የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ሴ/መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት1. ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት2. የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ ሎት3. የጽዳት እቃዎች፣ ሎት4. ፈርኒቸር ፣ሎት5. የስፖርት ትጥቅ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ካላቸዉ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መሳተፍ ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የ2017 ዓ.ም የስራ ግብር ሙሉ በሙሉ ከፍለው ያጠናቀቁ እና የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር አንድ በመቶ የጨረታ ሳጥኑ ከመከፈቱ ቀድሞ ገቢ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን የእቃ ዋጋ 10 በመቶ ወዲያዉኑ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ዉል በመዉሰድ የተጠየቁትን እቃዎች ጥራት ጠብቆ ኦሪጅናል ማቅረብ ይገባል፡፡
- ያሸነፉበትን እቃ ለማቅረብ ዉል የማይወሰድ ወይም ዉል ከወሰደ በኋላ እቃዉን የማያቀርብ ተጫራች ቢያጋጥም መ/ቤቱ ለዉል ማስከበሪያ የያዘዉን ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ መውረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ እስከ 1ዓመት ለሚደረስ ጊዜ በጨረታ እንዳይሳተፍ የማገድ ስልጣኑን ለመጠቀም ይገደዳል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የማወዳደሪያ ዋጋ ሲሞላ ሁለት ኦርጅናል በሁለት ፓስታ ታሽጎ ማስገባት ከጨረታዉ እንዲሰረዝ ይደረጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ ሳጥኑ መግባት ያለበት ኦርጅልናል እና ኮፒ ሆኖ በሁለት ፖስታ ታሽጎ ከፖስታዉ ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ ተጽፎ ከሳጥኑ ዉስጥ መግባት አለበት ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ) በመክፈል ከመ/ሰ/ከ/አስ/ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ከዋና ገንዘብ ያዥ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የንግድ ፈቃዱን የማይመለስ 1 ኮፒ የግብር ከፋይ ምዝገባ 1 ኮፒ፣ ቫት (ቲኦቲ) የምስክር ወረቀት የማይመለስ 1 ኮፒ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ታስቦ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ድረስ የመ/ሰ/ከ/ዝ//ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 210 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት አለባቸው ፡፡
- ጨረታዉ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታዉ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸዉ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ በነጠላ ዋጋ መሙያ ላይ ስርዝ ድልዝ አድርጎ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ሊደረግ ስለሚችል በጥንቃቄ መሙላት ይጠበቅበታል፡፡
- ጨረታው በሎት ወይም በጥቅል ድምር የሚካሄድ ስለሆነ ተጫራቾች በጥንቃቄ ሊሞሉ ይገባል፡፡
- የሚቀርቡው እቃዎች በተጠየቀዉ እስፔስፊኬሽን መሰረት መሆንይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታዉ ያሸነፈዉ ግለሰብ የሚያቀርበዉን እቃ ጽ/ቤቱ ድረስ የሚያመጣዉ በራሱ ወጭ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ለበለጠ መረጃ በስ. ቁጥር 033 220 1005 ወይም 09 14 45 28 92 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የመካነ ሠላም ከተማ አስተዳደር ገ/ጽ/ቤት

