ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ  ሰብል ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
24

በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ የ2018/2019 ምርት ዘመን ሎት 1. 5,000 ኩ/ል ነጭ በቆሎ ሰብል፣ ሎት 2. 5,000 ኩ/ል ነጭ በቆሎ ሰብል መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ  ተወዳዳሪዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የስራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸዉ፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየኑ ግዥና ፋይናንስ ዲቪጅን መውሰድና ዋጋ ሞልተዉ በማሽግ  ፖስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ11 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እና በ11ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ የመክፈቻ ቀን በእለቱ በ11ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጓለም፡፡
  6. ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. አሸናፊ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ ጀምሮ በእትዮጲያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የደንብ ዋስትና የተወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ማስከበሪያ ማሰገባትና ዉል መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  8. የማንሻ ቦታ ቡሬ ከተማ 04 ቀበሌ የሚገኘው መጋዝን ሲሆን የመጫኛና ልዩ ልዩ ወጪዎችን ገዥ የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  9. በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተገለጹ ነገሮችን ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥ እና ሽያጭ መመሪያ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 774 06 40 /10 32 በመደወል ወይም በአካል በመገኘት መስተናገድ ይችላሉ፡፡
  11. ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- የመክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀንና ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እናሳስባለን፡፡

የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒዬን ኃ.የተ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here