የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
26

በሰሜን ጎንደር ዞን የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በሴ/መ/ቤቶች መጋዝን ውስጥ የሚገኝ 1ኛ አሮጌ የቴዮታ መኪና ጎማ፣ 2ኛ አሮጌ የቴዮታ ባትሪ እንዲሁም 3ኛ አሮጌ የብረት በርሚል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ማንኛውም ግለሰብ መወዳደር ይችላል፡፡
  2. መነሻ ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. የዕቃ አይነትና ዝርዝር መገለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 8 በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ማለትም በአማረኛ የተተረጎመ ሲፒኦ ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመሂ 1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ከመጋቢት 14/2018 ዓ/ም እስከ መጋቢት 28/2018 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከመጋቢት 14/2018 ዓ/ም እስከ መጋቢት 28/2018 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ን/አስ ቢሮ ቁጥር 10 መጋቢት 29/2018 ዓ/ም 8፡00 ታሽጎ 8፡15 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኝም ባይገኙም የጨረታ ከፈታ ስርዓቱን አያስተጓጉለውም፡፡
  9. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ ሊኖረው አይፈቀድም ካለውም ፓራፍ ይደረግበት፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የእቃዎቹ ርክክብ የሚፈጸመው ጃናሞራ ወረዳ ከአራቱ ንብረት ክፍል ሲሆን አጠቃላይ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሲሆን እቃውን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች ትራንስፖርት እንዲሁም ማውረጃና መጫኛ አስበው መሙላት አለባቸው፡፡
  14. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 294 00 23 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here