በድጋሜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
42

ቁጥር 16/2018

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃዎችን ፈቃድ ያለቸዉን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታዉ ለመወዳደር የሚፈለጉ ድርጅቶች፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት፣ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ  ብር 300 (ሶስት መቶ  ብር) በመግዛት  አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 106 መዉሰድ  ይችላሉ፡፡ ሰነዶችን በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን በ16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡
  4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተመሰከረለት (ስፒኦ)፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚፈለጉትን የኤሌክትሮ መካኒካል እቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፊኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን    ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here