በአብክመ ጤና ጥበቃ ቢሮ የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተያዘው 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያሰራቸው ስራዎች ሎት1. የውስጥ ለውስጥ መንገድ መስሪያ፣ የካርድ ክፍል ማስፋፊያ እና የበር ታፔላ መገንቢያ አገልግሎት የሚውል ማቴሪያል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (ቲን )ያላቸዉ፡፡
- ግዥው ብር ከ200,000 (ሁለት መቶ ሽህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- የሚገዙ እቃዎች እና የሚሰሩ ስራዎች ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት እቃዎች ብር ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በማሸግ ማስያዝ እና በጥቃቅን መ/ቤት የተደራጁ ከሆኑ ካደራጃቸው መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ በአድራሻችን በመፃፍ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚቀጥሉት 5 የሥራ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በተዘጋጀዉ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 2፡59 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቡሬ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግ/ፋ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሸጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ሆኖም ጨረታዉ በመሰረዙ ምክንያት ተጨራቾች ላወጡት ዋጋ ሆስፒታሉ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት ብር 20,000 (ሃያ ሽህ) እና በላይ ከተፈጸመ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ሶስት በመቶ ይቀነሳል፡፡
- ተጫራቾች ለግዥ መመሪያ ተገዥ መሆን ይጠበቅበቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ በመፈረም እና የድርጅቱን ማህተም እና አድራሻ አድርገው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች አሸናፊው ተለይቶ ውል ከተያዘ በኋላ በራሱ ወጪ እስከ ቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ንብረት ክፍል ድረስ አምጥቶ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
- የጨረታው አሸናፊ መሆን የሚችለው በተጫረቱበት ዘርፍ በጥቅል ዋጋቸው ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ነው፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 0576 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

