የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ሎት1. የመንገድ ማሽነሪ ኪራይ፣ ሎት2. በሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነት ፕሮጀክት የውሃ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የሚሞሉት ዋጋ መጠኑ ብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም በዋ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
- ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ 9፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የበአል ቀን ከሆነ ስዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200 ብር በመግዛት ለጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡ እንዲሁም አሸናፊነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ አስይዘው ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ካስፈለጋቸው በስልክ ቁጥር 09 20 01 39 41 ወይም 09 80 51 37 26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

