0
8

የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሎት1. በሰቆጣ ቃል ኪዳን ስምምነት ፕሮጀክት ለመስኖ አገልግሎት ምንጭ ጠለፋ ስራ፣ ሎት2. ቆርቆሮ በቆርቆሮ የሆነ ስቶር ግንባታ ስራ  ለማሰራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተጠየቁትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡

  1. ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ) እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ለጨረታዉ የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች በየስራ ዘርፋቸው ለሎት1 ደረጃ 5 እና በላይ ለሎት2 ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣ በ22ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ታሽጎ 9፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በግ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በጨረታ ሂደቱ በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዐል ቀን ከሆነ ስዓቱ እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራቾች በ2014 ዓ/ም ተሻሽሎ የወጣውን መመሪያ ጨምሮ በሚሞላው ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም አሻሚ የሆነ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ እና ያልተሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር በመግዛት በጨረታ ሰነዱ ላይ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የገዙትን ሙሉ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. የጨረታ ማስከበሪያ ሁለት በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸወል፡፡
  10. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠ/ዋጋ 10 በመቶ በተረጋገጠና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ፤በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፡፡
  12. ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 09 20 01 39 41 ወይም 09 80 51 37 26 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የዋድላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here