ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
10

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ በዞኑ የሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለሚገለገሉባቸው ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል ዘይት ግሪስና ቅባት የኮንትራት ግዥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ዓመታዊ የኮንትራት ውል ወስዶ በሚፈለግበት ጊዜ አቅርቦቱን ማግኘት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ፡-

  1. በዘርፉ የሚመለከተው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማዕ/ጎን/ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 22 በመምጣት የተሟላ የጨረታውን ዝርዝር ማስታወቂያ እና ሙሉ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታው ዝርዝር መግለጫና የተሟላ የጨረታ ማስታወቂያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ይገኛል፡፡
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚውል ሲሆን በ16 ቀን በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በተገለፀው ቀንና ሰዓት ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 20 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 111 13 09 /04 20 ፋክስ ቁጥር 058 111 20 41 መደወልና ፋክስ ማድረግ ይችላሉ፡፡

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ገንዘብ መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here