ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
28

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ የሚገኘው የደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከተያዘዉ ከመሰረተ ልማት ከውጭ መደብ 6324 መሰረት በከተማችን ዉስጥ አሰፓልት እየተሰራ ስለሆነ የመንገድ ዳር ኮሪደር ለማሰራት በደረጃ 5 ከዚያን በላይ ያላቸዉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በዘርፋ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሠነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚሰራዉ ኮሪደር ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 04 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የኮሪደሩ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. የጨረታ ሠነድ የሚሸጥበት ቦታ ደብረ ኤልያስ ከተማ መሪ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 ነው፡፡
  9. ጨረታው የሚቆየው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የገዙትን ሠነድ መመለስ የሚችሉት ጋዜጣው ከወጣበት እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ15ኛው ቀን 11፡30 የጨረታ ሳጥኑ የታሽጋል፡፡
  11. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾችም ሆነ ወኪሎቻቸው ባይገኙም እንኳን ጨረታው በእለቱ ደብረ ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  13. የተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ተነባቢ መሆን ይኖርበታል፡፡
  14. የተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  15. የሚሰራዉ ቦታ ከወ/ሮ ትዛለች ተመስጌን ቤት እስከ ጊዜ ወፍጮ ቤት ድረስ ያለውን ኮሪደር ነው፡፡
  16. በኮሪደር ስራ መልካም አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  17. ውድድሩ በሎት በጥቅል ዋጋ የሚለይ ይሆናል፡፡
  18. መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ቦታው ከምሥራቅ ጎጃም ዞን ከደብረ ማርቆስ ከተማ በምዕራብ አቅጣጫ 42 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ነው፡፡
  20. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለጋችሁ በከተማው መሪ ማዘጋጃ ቤት በአካል ቀርበው ወይም በስልክ ቁጥር 058 250 02 30 /668 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የደብረ ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here