በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
29

በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን መምሪያ የዳውንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ር ቡድን ፤የዳዉንት ወረዳ ስራና ስልጠና ተቋም በመደበኛ በጀት ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለሚያስገነባዉ የኤሌክትሪክ ወርክ ሾፕ፣ የእንጨት ስራ ወርክ ሾፕ ግንባታ እና ለዳውንት ወረዳ አስተዳደር ምክር ቤት  ህንጻ ቀሪ ስራዎችን ለማሰራት ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ  የዳውንት ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ር ቡድን ለግንባታዉ ከደረጃ አራትና ከዚያ በላይ ያሉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልተው እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን)፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ኦርጅናልና ኮፒ መረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታስክ (ቫት) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚሙሉትም ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ግንባታ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሽህ ብር) ጠቅላላ  ብር 450,000 (አራት መቶ ሀምሳ ሽህ ብር)  በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትእዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ህገዊ ደረሰኝ ተቆርጦ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. ማንኛውም ግዥ ከብር 20,000 (ሀያ ሽህ ብር) በላይ  እና ለአገልግሎት ግዥ ከብር 10,000  (አስር ሽህ ብር)  በላይ 3 በመቶ የቅድመ ግብር ተቀንሶ ገቢ ይደረጋል፡፡
  5. ተጫራቾች ከላይ የተገለፁትን ግንባታዎች የፋይናሽያል የጨረታ ሰነድ እና ቴክኒካል ሰነድ ቢሮ ቁጥር 15 እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው  ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እና የንግድ ፈቃድ መረጃቸውን ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በጥንቃቄ  በማሸግ  የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት  የሚቆይ ሲሆን  እስከ 22 ተኛው ቀን 3፡30 ድረስ  ዘወትር በስራ ሰዓት ዳ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 15 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት  ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለዚሁ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ፋይናሻልና ቴክኒካል ሰነድ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ማለትም ሚያዚያ 12/2018 ዓ.ም ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡                                   ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉለውም ፡፡
  8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው የስራ ዝርዝር መገለጫ መሰረት በሰነዱ በእያንዳነዱ በግልጽ ዋጋውን መሙላት እና የድርጅታቸውን አድራሻ፣ ስም፣ ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች በሞሉት የግንባታ ሰነድ ላይ በነጠላ ዋጋም ሆነ በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑ ማወቅ አለባቸው፡፡
  10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ካሉ በክልሉ የግዥ አዋጅ 179/2003 እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ከጨረታ ውጭ እንደሚደረጉ ያስያዝቱን የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ እንደሚደረግ እና  በተመሳሳይ ሌላ ጨረታ እንደይሳተፉ ይደረጋል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ውድድሩ በጠቅላላ ድምር ዋጋ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡
  12. ተጫራቾች በጨረታው ውጤት ቅር ከተሰኙ የጨረታ ውጤቱ በማስታወቂያ ቦርድ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅሬታቸውን በየደረጃው ላለ የፋይናንስ ተቋማት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
  1. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ቢፈልጉ ቢሮ ቁጥር 15 ደረስ በመምጣት በስልክ ቁጥር 033 241 91 37 /በመደወል  መጠየቅ ይችላሉ፡፡

   የዳውንት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here