እነሆ መላ!

0
10

በየእለቱ ከሦስት ስኒ ወይም ብርጭቆ ያልበለጠ ቡና ወይም ሻይ የሚጠጡ ሰዎች እድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ ሊከሰትባቸው የሚችል የመርሳት እና የማገናዘብ አቅም ማሽቆልቆልን በመከላከል የአእምሮ ጤናን መጠበቅ እንደሚያስችላቸው  ሳይንስ ዴይሊ ድረ ገጽ ሰሞኑን አስነብቧል፡፡

በአሜሪካ ቦስተን የሚገኘው የማሳቹሴት እና ብሪንግሀም ሆስፒታል ተመራማሪዎች ከሌሎች አቻ ተቋማት ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ከ130 ሺህ በላይ የናሙና ጥናት ተሳታፊዎችን  ለ40 ዓመታት በመከታተል ውጤቱን መቀመር ችለዋል፡፡ በዚህም 18 በመቶ ቡና እና ሻይ የጠጡት ካልጠጡት ያነስ በመርሳት በሽታ ሳይያዙ መቅረታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ የማገናዘብ አቅም መቀነስን በተመለከተም ቡና የማይጠጡት ዘጠኝ ነጥብ አምስት በመቶ ሲጠቁ የጠጡት ሰባት ነጥብ ስምንት በመቶ ሆኖ ውጤቱ ተመዝግቧል፡፡ ይህም ቡና ወይም ሻይ በመካከለኛ መጠን መጠጣት ጠቃሚነቱን እንደሚያመላክት ነው የጥናቱ ውጤት ያረጋገጠው፡፡

የአእምሮ ጤና ማጣት በሽታ ከጀመረ በኋላ ለማዳን ህክምናው ውስን እና ከፍተኛ ወጪ እንደሚጠይቅም ነው የድረ ገጹ ጽሁፍ ያመላከተው፡፡ ተመራማሪዎቹ በሻይም ሆነ በቡና ውስጥ የሚገኘው “ካፊን” የተሰኘው ንጥረ ነገር የአንጐል ጤናን  ለመጠበቅ ያለው አበርክቶ የጐላ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው አስረድተዋል፡፡

በመጨረሻም የምርምሩን ደረጃ ከፍ ባለመልኩ  የተገነዘቡት ተመራማሪዎቹ የ“ካፊን” መጠኑ በቡና ወይም በሻይ ውስጥ ከፍ ቢልም የሚያደርሰው ጉዳት የተጋነነ አለመሆኑን ማረጋገጣቸውን ድረ ገጹ ጠቁሟል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመጋቢት 21  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here