ጥቃት አድራሹ ድብ

0
12

በካሊፎርኒያ የቴሊቪዥን ዘጋቢዋ በተለያዩ የሰዎች መኖሪያ ቀጣና ድብ ድንገት በመግባት ጥቃት እያደረሰ መሆኑን በቀጥታ ስርጭት በምተቀርብበት ትእይንት ድብ በአካል መታየቱን  ዩፒ አይ ድረ ገጽ ሰሞኑን ለንባብ አብቅቶታል::

“ኬቲ ኤል ኤ” ለተሰኘው የቴሌቪዥን ጣቢያ የቀጥታ ስርጭት ዘጋቢዋ ኢሪን ሜየር ድብ ቀደም ባሉት ቀናት ጥቃት ማድረሱን በማቅረብ ላይ እያለች ሳይታሰብ ድብ ከትእይንቱ ጀርባ በአካል መታየት ችሏል::

ዘጋቢዋ ድቡን  ስርጭት ላይ እያለች እንደተመለከተችው “አዎ! ሁላችንም ያንን ድብ በቀኝ በኩል እያየነው ነው” የሚል ድንገተኛ አስተያየት ስትሰጥ ከቀረፃው ጀርባ የነበሩ ባልደረቦችዋ “ዋው!” የሚል የድንጋጤ ድምፅ ሲያሰሙ ለአድማጭ ጆሮ ደርሷል::

የቴሌቪዥን ዘጋቢዋ ኢሪን ሜየር በቀጣናው ውሻዋን ይዛ ስትንቀሳቀስ የነበረች ኗሪ ውሻዋ ድንገት ድብ ባየበት ወቀት ተወርውሮ በላይዋ ላይ  በመውጣቱ  ወደቃ ጉዳት እንደደረሰባት መጠየቅ ካቀረበችላቸው ባለ ስልጣናት መረዳቷን ጠቁማለች:: ነገር ግን በቀጥታ ስርጭቱ ላይ የታየው ድብ ቀደም ብሎ ውሻቸውን ይዘው ሲዟዟሩ ከነበሩት ኗሪ ጋር ፊት ለፊት የተያየ ለመሆኑ እርግጠኛ አለመሆናቸውን ነው ያስረዱት::

የቀጣናው ባለስልጣናት “ድብ በቀጣናው ግጭት ያደርሳል? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ እማኝነታቸውን አረጋግጠዋል:: ሁነቱ በመኖሪያ አካባቢያቸው የደን መጨፍጨፍ ወይም የአየር ንብረት ለውጥ ያስከተለው ዳፋ ሊሆን እንደሚችልም ነው የጠቆሙት::   በመጨረሻም የግዛቱ የአሳ እና የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣናት ኗሪዎች ድብ ሲያጋጥማቸው ርቀታቸውን እንዲጠብቁ፣ እንስሳቱን ከመመገብ እንዲቆጠቡ እና የሚጣል ቆሻሻን በተዘጋጀ ጠንካራ ማጠራቀሚያ እንዲያኖሩ መክረዋል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመጋቢት 21  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here