ክሩገር ብሔራዊ ፓርክ

0
9

ክሩገር ብሔራዊ ፓርክ በደቡብ አፍሪካ ከዋና ከተማዋ ጆሀንስበርግ በግምት ከ400 እስከ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው:: የፓርኩ ስፋትም 19 ሺህ 485 ኪሎ ሜትር ስከዌር ተለክቷል::

ፓርኩ አገሪቱ ካሏት ዘጠኝ ግዛቶች በሁለቱ ሊምፖፖ እና ማፑ ማላንጋ ውስጥ የተካለለ ነው:: አብዛኛው የፓርኩ ቀጣና መገኛ ከባህር ወለል በላይ በምሥራቅ 200 ሜትር እስከ ደቡብ ምዕራብ 840 ሜተር ከፍታ ያለው መሆኑም ተለክቷል::

በፓርኩ ከእፅዋት 400 ዝርያዎች  መኖራቸው ተረግግጧል:: ሳር ለበስ ሜዳ እና ደን የመልካ  ምድሩ ገጽታ አካል ናቸው::

ከዱር እንስሳት 147 የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎች፣ 114 የተሳቢ እንስሳት፣ 49 የአሳ እና 34 በውኃ እና በየብስ የሚኖሩ “አምፊቢያንስ” ዝርያዎች መገኘታቸውን ድረ ገፆች አስፍረዋል::

በአካል መጠን ግዝፈት ካላቸው አውራሪስ፣ ዝሆን፣ ጉማሬ፣ አንበሳ፣ አቦሸማኔ፣ የሜደ አህያ፣ ቀጭኔ፣ የሜዳ ፍየል፣ ዓዞ እንደሚገኙ ነው የሰፈረው- በድረ ገፆች::  የእያንዳንዳቸው ብዛት ከተጠቆሙት 1 ሺህ 500 አንበሶች፣ 12 ሺህ ዝሆን፣ 2 ሺህ 500 ጐሽ፣ 1 ሺህ አቦ ሸሜኔ እና 5 ሺህ አውራሪስ እንደሚገኙ ባለሙያዎች ግምታቸውን አስፍረዋል::

በፓርኩ ቀጣና እንደየጐብኚዎች ፍላጐት እና ምርጫ ሆቴሎች፣ የእንግዳ ማረፊያዎች ተዘጋጅተዋል::

ወደ ፓርኩ በተሽከርካሪ ኮጆሀንስበርግ፤ በአውሮኘላን ኮጀርጅ ወይም ኤልዛቤት አየር ማረፊያ በጆሀንስበርግ ወይም ከደርባን ወደ ክሩገር ማፑ ማላንጋ አየር ማረፊያ መድረስ ይቻላል::

ለፓርኩ ዘላቂነት ከቀጣናው ውጪ የመጡ ለውኃ እጥረት የሚዳረጉ መጤ ዝርያዎች ስጋት መሆናቸውም ተጠቅሷል::

ለዘገባችን በመረጃ ምን ምንጭነት ስቶሪ ኦፍ ክሩገር፣ ክሩገር ናሽናል  ፓርክ እና ሳንፓርክ ዶት ኦርግ ድረ ገፆችን ተጠቅመናል::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የመጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here