በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የኤሌክትሪክ እቃዎች ፣የኦአር ጫማ ፣የሕክምና እቃዎች፣ ጀኔሬተር ሙሉ ሰርቪስ፣ የፅህፈት መሳሪያ እና ኮምፒዩተር እና የኮምፒተር ተዛማጅ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ተጫራቾች እቃዎችን ወይም አገልግሎቾችን ለማቅረብ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያወጡ፣ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዦች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማረኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
- በጨረታው መጫረት የምትፈልጉ በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡0ዐ ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግ ጨረታውን ላወጣው መስሪያ ቤት በፅሁፍ ወይም በስልክ ቁጥር 058 661 03 3ዐ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤትም የተጠየቀውን ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሁፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀናት በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድ ቅዳሜና በአል ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተጠየቀው ስዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች አሸናፊው ከተለየ በኋላ የሚመለስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 4,000 (አራት ሽህ ብር) ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል

