ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
19

የጨረታ ቁጥር አብክመ/ስቪእና ቤተሰብ ም/አገ/ብ/ግ/ጨ//07/2018

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት  ለአገልግሎት የሚውሉ የክብር መዝገብ ህትመት ለማሳተም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አገልግሎቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች (ሎቶች) አንድ በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ስቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ከተጠቀሱት ዕቃዎች ተጫራቾች የተጫረቱበት እቃ ሰነድ እስከ 16ተኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ስቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 406 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናቶች ክፍት ሁኖ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ይታሸግና በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. አገልግሎት መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 406 ድረስ በአካል በመገኘት /በስልክ ቁጥር 058 320 3158 በመደወል ወይም ፋክስ 058 320 1183 ፖ.ሳ.ቁ 965 በመላክ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here