የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
28

የቡሬ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታ ስለመያዝ በደነገገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 መመሪያ ቁጥር 01/2005 መሰረት በ2018 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፦

  1. የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 12 በመምጣት የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ዓይነት መደበኛ
  3. የጨረታ ሰነድ መግዣ ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  4. የጨረታው ሰነድ መሸጫ ጊዜ የሚያልቀው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ነው፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ቡሬ ከተ/አስ/ር/መ/ጽ/ቤት ግቢ ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በቡሬ ከተ/አስ/ር/መ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ ለድርጅት 5 በመቶ ለመኖሪያ 5 በመቶ በማቅረብ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ አሸናፊው ከተለየ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  8. የግንባታ ደረጃ ለድርጅት G+2 እና ከዚያ በላይ ለመኖሪያ G+0 ከዚያ በላይ የቦታው አገልግሎት በእያንዳንዱ ምድብ ከሰነዱ ጋር በሚሸጠው ሰነድ ሰንጠረዥ ላይ የተቀመጠው ይሆናል፡፡ ለጨረታ የወጣው የቦታ ብዛት ድርጅት 05 መኖሪያ 25 ጠቅላላ ድምር 30 ነው፡፡
  9. በዚህ ያልተገለፀ ሀሳብ ካለ በአዋጁ ቁጥር 721/2004 መሰረት የሚስተናገድ ይሆናል፡፡
  10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 16 23 /058 774 03 66 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

የቡሬ ከተማ አስ/ር መሬት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here