በምዕ/ጉጃም ዞን የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በቡሬ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ንብረት ክፍል የሚገኘውን የተለያዩ ብረታ ብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ) ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የታደሰ የሙያ ፈቃድ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁጥር ከ1-4 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ዋናውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ያገኛሉ ሆኖም ግን ብረታ ብረቶቹን በአካል ማየት ከፈለጉ ቡሬ /ዙ/ወ/ ግብርና ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመጋቢት 28/2018 ዓ.ም እስከ ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በሆነ በታሸገ ፖስታ ዋና እና ፎቶ ኮፒው ቡ/ዙ/ወ/ገ/ ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ጨረታው ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት የአንዱን ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ድምር በመሙላት የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመውሰድ ብር 200 (ሁለት መቶ ) በመክፈል ሰነዱን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያው ያልተካተቱ ሃሳቦች በግዥ መመሪያው ቁጥር 1/2003 እና በሌሎች በተሻሻሉ የግንባታ የግዥ መመሪያዎችን የሚገዙ ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ/ን/አስ/ ቡድን በአካል በመገኘት በስልክ ወይም ቁጥር 058 774 0237 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቡሬ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

